Топ-100
Back

ⓘ ኅዳር ፲፮                                     

ⓘ ኅዳር ፲፮

በዚህ ዕለት በዓለም ዙሪያ ብዙ ተፈጥሮአዊ ሁከቶች የብዙ ሕዝቦችን ሕይወት ማጥፋታቸው በታሪክ ተመዝግቧል። ለምሣሌ፦

 • በ፲፫፻፴፮ ዓ.ም. በሰሜናዊ የሜዲተራንያን ባሕር በተለይም ከኢጣልያ በስተምዕራብ በሚገነው የቲሬኖ ባሕር ሥር የተነሳ የመሬት እንቅጥቅጥ ያስከተለው የባሕር መናወጥ tsunami፣ አካባቢውን አጥፍቷል።
 • በ፲፮፻፷ ዓ.ም. በአሁኗ አዘርባይጃን አገር ውስጥ ሼምካ በተባለ ሥፍራ የመሬት እንቅጥቅጥ ሰማንያ ሺህ ሰዎችን ገድሏል።
 • በ፲፮፻፺፮ ዓ.ም. በደቡብ ብሪታንያ ታላቅ አውሎንፋስ ተነስቶ ዘጠኝ ሺህ ሰዎችን ገድሏል።
 • በ፲፯፻፶፪ ዓ.ም. በሜዲተራንያን ባሕር አካባቢ የተነሳ የመሬት እንቅጥቅጥ ቤይሩትንና ደማስቆን ሲያወድም ከሠላሣ እስከ አርባ ሺህ ሰዎች ፖተዋል።
 • በ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. ከባሕር ሥር የተነሳ የመሬት እንቅጥቅጥ ሱማትራን ሲያወድም ያስከተለው የባሕር ሞገድ የኢንዶኔዚያን ጠቅላላ ጠረፍ አጥለቅልቆታል።
 • በ፲፰፻፴፪ ዓ.ም. በሕንድ አገር ላይ የተነሳው ጥቅል አውሎንፋስ የኮሪንጋን ከተማ ሲያወድም፣ የተከተለው የውቅያኖስ ሞገድ ደግሞ ወደሃያ ሺህ የሚጠጉ መርከቦችን ጠራርጓል። ወደ ሦሥት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ሞተዋል።
 • በ፲፱፻፲፱ ዓ.ም. በአሜሪካ ታሪክ ሃይለኛው የኅዳር ጥቅል አውሎንፋስ ተነስቶ በመካከለኛ - ምዕራባዊ ግዛቶች በጠቅላላው ሰባ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ ከአራት መቶ በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የጉዳቱ ብሶት በአርካንሳስ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ‘ሀርብ ስፕሪንግስ’ ላይ ሲሆን አምሣ አንዱ ሟቾች ከዚያው ግዛት ነበሩ።
 • በ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. በሰሜናዊ ምሥራቅ አሜሪካ በሰዐት መቶ ስድሳ ኪሎሜትር ፍጥነት ያለው ንፋስ ያስከተለው የበረዶ ነበልባል የሦስት መቶ ሃያ ሦስት ሰዎች የሞት ምክንያት ሆኗል።
 • በ፲፱፻፹ ዓ.ም. በሰዐት ሁለት መቶ ስድሳ አምስት ኪሎሜትር ፍጥነት ባለው ነፋስ የተነዳችው" ኒና”፣ Super Typhoon Nina የተባለችው አውሎንፋስ የፊሊፒን ደሴቶች ላይ የከሰተችው ቁጣ ወደ አንድ ሺህ ሠላሣ ሰዎችን ገድሏል።
 • በ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. የበረዶ ምታት በመካከለኛው የአሜሪካ ግዛቶች ላይ ሃያ ስድስት ሰዎችን ሲገል፤ በፍሎሪዳ ደግሞ በሰዐት መቶ አርባ አምሥት ኪሎሜትር ፍጥነት ያለው የነፋስ ምታት ተነስቶ ዛፎችን ፈነቃቀለ ሌላም ጉዳት አደረሰ።
 • በ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. በባኩ ኃይለኛ የመሬት እንቅጥቅጥ ተከስቶ ሃያ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ ከአራት መቶ በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
                                     

1. ሌላ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

 • ፲፰፻፷ ዓ.ም. - የስዌድ ተወላጁ አልፍሬድ ኖቤል የዲናሚት ፈጠራውን የባለቤትነቱን መብት አስመዘገበ።
 • ፲፱፻፶፮ ዓ.ም. - በዳላስ፣ ቴክሳስ ላይ በሰው እጅ የተገደሉት ሠላሣ አምሥተኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በአርሊንግተን ብሔራዊ መቃብር በታላቅ ሥነ ስርዐት ተቀበሩ። በዚሁም የቀብር ስርዐት ለመሳተፍ ከዓለም ዙሪያ ብዙ መሪዎች መጥተው ነበር። ከነዚህም መሃል የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ሻርል ደ ጎል፤ የአየርላንድ ፕሬዚደንት ደ ቫሌራ፤ የምዕራብ ጀርመን ቻንስለር ኤርሃርድና የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ይገኙበት ነበር።
 • ፲፱፻፶፰ ዓ/ም - በእስራኤል፤ ፈረንሳይ፤ ብሪታኒያ፤ ምዕራብ ጀርመን፤ ስዊድን እና ጃፓን መንግሥታት ዕርዳታ የተገነባው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሕንፃ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ።
 • ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. - በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው ታላቁ ድርቅና ረሐብ እርዳታ እንዲሆን በብሪታንያ ሠላሣ ስድስት የሙዚቃ ባለሙያዎች" ባንድ ኤይድ” በሚል ስም ተሰባስበው፤" የክርስቶስ ልደት መሆኑን ያውቁታል ወይ?” Do They Know Its Christmas የተባለውን ዘፈን ቀረጹ።
 • ፲፱፻፸፱ ዓ.ም. - በአሜሪካ የ”ኢራን ኮንትራ አፌር” የተባለው የፖለቲካ ቅሌት ፈነዳ። ፕሬዚደንቱ ሮናልድ ሬጋን እና አቃቤ ሕጉ በስልጣን የነበሩ ሽርከኞች በምስጢር ለኢራን የጦር መሣሪያ እየሸጡ የሚገኘውን ትርፍ ደግሞ ለኒካራጓ ሽብርተኞች በምስጢር እንዳስተላለፉ ይፋ አደረጉ። ሁለት ባለሥልጣናት ወዲያው እንደተሻሩም ፕሬዚደንቱ ገለጹ።
 • ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. - የቼኮስሎቫኪያ ፌዴራላዊ ሸንጎ አገሪቱ ከሚቀጥለው የአውሮፓውያን ዘመን መግቢያ ጀምሮ ለሁለት እንድትከፈል ደነገገ። ይሄም የአሁኖቹን የቼክ ሪፑብሊክ እና ስሎቫኪያ ሉዐላዊ አገሮችን የፈጠረው ድርጊት ነው።
Free and no ads
no need to download or install

Pino - logical board game which is based on tactics and strategy. In general this is a remix of chess, checkers and corners. The game develops imagination, concentration, teaches how to solve tasks, plan their own actions and of course to think logically. It does not matter how much pieces you have, the main thing is how they are placement!

online intellectual game →